• 1. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤

  • 2. ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት!

  • 3. ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?

  • 4. ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤

  • 5. ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡)

  • 6. ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤

  • 7. እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡

  • 8. ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤

  • 9. መኖሪያው ሃዊያህ ናት

  • 10. እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?

  • 11. (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡

ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo