• 1. ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤

  • 2. ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤

  • 3. ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤

  • 4. መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤

  • 5. ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡

  • 6. አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?

  • 7. በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡

  • 8. በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡

  • 9. ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡

  • 10. በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤

  • 11. የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡

  • 12. የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡

  • 13. እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡

  • 14. ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡

  • 15. በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡

  • 16. እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡

  • 17. የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?

  • 18. ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?

  • 19. (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡

ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo