• 1. ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤

  • 2. ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤

  • 3. ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤

  • 4. በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡

  • 5. ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡

  • 6. በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡

  • 7. የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

  • 8. የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

ሼር ያድርጉ
logo
logo
logo
logo