HARUN YAHYA
Amharic / አማርኛ
AM
ቁርኣን
سورة الواقعة
1. መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡
2. ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡
3. ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡
4. ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡
5. ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡
6. የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ
7. ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡
8. የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
9. የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
10. (ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
11. እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡
12. በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡
13. ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
14. ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡
15. በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡
16. በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡
17. በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡
18. ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡
19. ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡
20. ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡
21. ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡
22. ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡
23. ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡
24. በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡
25. በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡
26. ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡
27. የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!
28. በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡
29. (ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡
30. በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡
31. በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡
32. ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡
33. የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡
34. ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡
35. እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡
36. ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡
37. ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡
38. ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡
39. ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
40. ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
41. የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡
42. በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡
43. ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡
44. ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡
45. እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡
46. በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡
47. ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን?
48. «የፊተኞቹ አባቶቻችንም?»
49. በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡
50. «በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡
51. «ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ!
52. « ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡
53. «ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡
54. «በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡
55. «የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡»
56. ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡
57. እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?
58. (በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን?
59. እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን?
60. እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
61. ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡
62. የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን?
63. የምትዘሩትንም አያችሁን?
64. እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?
65. ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡
66. «እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡
67. «በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡
68. ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን?
69. እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?
70. ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን?
71. ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?
72. እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን?
73. እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡
74. የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡
75. በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡
76. እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡
77. እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
78. በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
79. የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡
80. ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
81. በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?
82. ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን?
83. (ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡
84. እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡
85. እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡
86. የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡
87. እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡
88. (ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡
89. (ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡
90. ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡
91. ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡
92. ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡
93. ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡
94. በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡
95. ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡
96. የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡
ሼር ያድርጉ
1. ورَةُ الْفَاتِحَة
2. ورَةُ البقرة
3. سُورَةُ آل عمران
4. سورة النساء
5. سورۃ المائدة
6. سورة الأنعام
7. سورة الاعراف
8. سورۃ الانفال
9. سورة التوبة
10. سورة يونس
11. سورۃ ھود
12. سورة يوسف
13. سورة الرعد
14. سورة ابراهيم
15. سورة الحجر
16. سورة النحل
17. سورة الإسراء
18. سورة الكهف
19. سورة مريم
20. سورة طه
21. سورة الأنبياء
22. سورة الحج
23. سورة المؤمنون
24. سورة النور
25. سورة الفرقان
26. سورة الشعراء
27. سورة النمل
28. سورة القصص
29. سورة العنكبوت
30. سورة الروم
31. سورة لقمان
32. سورة السجدة
33. سورة الأحزاب
34. سورة سبإ
35. سورة فاطر
36. سورةيس
37. سورة الصافات
38. سورة ص
39. سورة الزمر
40. سورة غافر
41. سورة فصلت
42. سورة الشورى
43. سورة الزخرف
44. سورة الدخان
45. سورة الجاثية
46. سورة الأحقاف
47. سورة محمد
48. سورة الفتح
49. ورة الحجرات
50. سورة ق
51. سورة الذاريات
52. سورة الطور
53. سورة النجم
54. سورة القمر
55. سورة الرحمن
56. سورة الواقعة
57. سورة الحديد
58. سورة المجادلة
59. سورة الحشر
60. سورة الممتحنة
61. سورة الصف
62. سورة الجمعة
63. سورة المنافقون
64. سورة التغابن
65. سورة الطلاق
66. سورة التحريم
67. سورة الملك
68. سورة القلم
69. سورة الحاقة
70. سورة المعارج
71. سورة نوح
72. سورة الجن
73. سورة المزمل
74. سورة المدثر
75. سورة القيامة
76. سورة الانسان
77. سورة المرسلات
78. سورة النبإ
79. سورة النازعات
80. سورة عبس
81. سورة التكوير
82. سورة الإنفطار
83. سورة المطففين
84. سورة الإنشقاق
85. سورة البروج
86. سورة الطارق
87. سورة الأعلى
88. سورة الغاشية
89. سورة الفجر
90. سورة البلد
91. سورة الشمس
92. سورة الليل
93. سورة الضحى
94. سورة الشرح
95. سورة التين
96. سورة العلق
97. سورة القدر
98. سورة البينة
99. سورة الزلزلة
100. سورة العاديات
101. سورة القارعة
102. Aسورة التكاثر
103. سورة العصر
104. سورة الهمزة
105. سورة الفيل
106. سورة قريش
107. سورة الماعون
108. سورة الكوثر
109. سورة الكافرون
110. سورة النصر
111. سورة المسد
112. سورة الإخلاص
113. سورة الفلق
114. سورة الناس