61. سورة الصف - ቁርዓን
- 1. በሰማያት ውስጥ ያለው በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሠ፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
- 2. እላንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሠሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ?
- 3. የማትሠሩን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡
- 4. አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ኾነው በመንገዱ (በሃይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል፡፡
- 5. ሙሳም ለሕዝቦቹ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደእናንተ የአላህ መልክተኛ መኾኔን በእርግጥ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?» ባለ ጊዜ (አስታውስ፡፡ ከእውነት) በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው፡፡ አላህም አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡
- 6. የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደእናንተ (የተላክሁ) የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡
- 7. እርሱ ወደ ኢስላም የሚጥጠራ ሲኾን በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰውም ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡
- 8. የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው፡፡