54. سورة القمر - ቁርዓን
- 1. ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡
- 2. ተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ፡፡
- 3. አስተባበሉም፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፡፡ ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው፡፡
- 4. ከዜናዎችም በእርሱ ውስጥ መገሰጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መጣላቸው፡፡
- 5. ሙሉ የኾነች ጥበብ (መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አያብቃቁም፡፡
- 6. ከነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው (መልአክ) ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
- 7. ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ኾነው፤ ፍጹም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወጣሉ፡፡
- 8. ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸኳዮች ኾነው (ይወጣሉ)፡፡ ከሓዲዎቹ (ያን ጊዜ ምን ይላሉ?) «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ፡፡
- 9. ከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፡፡ ባሪያችንንም (ኑሕን) አስተባበሉ፡፡ «ዕብድ ነውም» አሉ፡፡ ተገላመጠም፡፡
- 10. ጌታውንም «እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ጠራ፡፡
- 11. ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን፡፡
- 12. የምድርንም ምንጮች አፈነዳን፡፡ ውሃውም (የሰማዩና የምድሩ) በእርግጥ በተወሰነ ኹነታ ላይ ተገናኘ፡፡
- 13. ባለ ሳንቃዎችና ባለሚስማሮች በኾነችም ታንኳ ላይ ጫንነው፡፡
- 14. በጥበቃችን ስር ኾና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረው ሰው ምንዳ (ይህንን ሠራን)፡፡
- 15. ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት፡፡ ከተገሳጭም አልለን?
- 16. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?
- 17. ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን?
- 18. ዓድ አስተባበለች፡፡ ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ!
- 19. እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በኾነ ቀን በኀይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው፡፡
- 20. ሰዎቹን ልክ ከሥሮቻቸው የተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው (ከተደበቁበት) ትነቅላቸዋለች፡፡
- 21. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?
- 22. ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?
- 23. ሰሙድ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡
- 24. «ከእኛ የኾነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያን ጊዜ በስህተትና በዕብደት ውስጥ ነን» አሉ፡፡
- 25. «ከኛ መካከል በእርሱ ላይ (ብቻ) ማስገንዘቢያ (ራእይ) ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» (አሉ)፡፡
- 26. ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደኾነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
- 27. እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትኾን ዘንድ ላኪዎች ነን፡፡ ተጠባበቃቸውም፡፡ ታገስም፡፡
- 28. ውሃውንም በመካከላቸው የተከፈለ መኾኑን ንገራቸው፡፡ ከውሃ የኾነ ፋንታ ሁሉ (ተረኞቹ) የሚጣዱት ነው፡፡
- 29. ጓደኛቸውንም ጠሩ፡፡ ወዲያውም (ሰይፍን) ተቀበለ፡፡ ወጋትም፡፡
- 30. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?
- 31. እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው፡፡ ወዲያውም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ ርግጋፊ ኾኑ፡፡
- 32. ቁርኣንንም ለመገንዘብ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?
- 33. የሉጥ ሕዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች፡፡
- 34. እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ (እነርሱንስ) በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው፡፡
- 35. ከእኛ በኾነ ጸጋ (አዳንናቸው)፡፡ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን፡፡
- 36. ብርቱይቱን አያያዛችንንም በእርግጥ አስጠነቀቃቸው፡፡ በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ፡፡
- 37. ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት፡፡ ወዲያውም ዓይኖቻቸውን አበስን፡፡ «ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ» (አልናቸው)፡፡
- 38. በማለዳም ዘውታሪ የኾነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው፡፡
- 39. «ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ» (ተባሉ)፡፡
- 40. ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገሳጭም አልለን?
- 41. የፈርዖንንም ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡዋቸው፡፡
- 42. በተዓምራቶቻችን በሁሏም አስተባበሉ፡፡ የብርቱ ቻይንም አያያዝ ያዝናቸው፡፡
- 43. ከሓዲዎቻችሁ ከእነዚህ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለናንተ በመጽሐፎች ውስጥ (የተነገረ) ነፃነት አላችሁን?
- 44. ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉን?
- 45. ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይምመታሉ፡፡ ጀርባዎችንም ያዞራሉ፡፡
- 46. ይልቁንም ሰዓቲቱ (ትንሣኤ) ቀጠሮዋቸው ናት፡፡ ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት፡፡
- 47. አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው፡፡
- 48. በእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው በሚጎተቱበት ቀን «የሰቀርን መንካት ቅመሱ» (ይባላሉ)፡፡
- 49. እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡
- 50. ትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት አንዲት (ቃል) እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
- 51. ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፡፡ ተገሳጭም አልለን?
- 52. የሠሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው፡፡
- 53. ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተጻፈ ነው፡፡
- 54. አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው፡፡
- 55. (እነርሱም ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ቻይ የሆነው ንጉሥ ዘንድ ናቸው፡፡