85. سورة البروج - ቁርዓን
- 1. የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
- 2. በተቀጠረው ቀንም፤
- 3. በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡
- 4. የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡
- 5. የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡
- 6. እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡
- 7. እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡
- 8. ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡
- 9. በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡
- 10. እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡
- 11. እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
- 12. የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡
- 13. እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡
- 14. እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡
- 15. የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡
- 16. የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡
- 17. የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን?
- 18. የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡
- 19. በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡
- 20. አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
- 21. ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
- 22. የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡