102. Aسورة التكاثر - ቁርዓን
- 1. በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡
- 2. መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡
- 3. ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡
- 4. ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡
- 5. በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡
- 6. ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡
- 7. ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡
- 8. ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡