107. سورة الماعون - ቁርዓን
- 1. ያንን በምርመራው የሚያስተባብለውን አየህን? (ዐወቅከውን?)
- 2. ይህም ያ የቲምን በኀይል የሚገፈትረው፤
- 3. ድኻንም በማብላት ላይ የማያግባባው ሰው ነው፡፡
- 4. ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡
- 5. ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡
- 6. ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት፡፡
- 7. የዕቃ ትውስትንም (ሰዎችን) የሚከለክሉ ለኾኑት (ወዮላቸው)፡፡