109. سورة الكافرون - ቁርዓን
- 1. በላቸው «እናንተ ከሓዲዎች ሆይ!
- 2. «ያንን የምትግገዙትን (ጣዖት አሁን) አልግገዛም፡፡
- 3. «እናንተም እኔ የምግገዛውን (አምላክም አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡
- 4. «እኔም ያንን የተገዛችሁትን (ወደፊት) ተገዢ አይደለሁም፡፡
- 5. «እናንተም እኔ የምግገዛውን (ወደፊት) ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡
- 6. «ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ፡፡