1. ورَةُ الْفَاتِحَة - ቁርዓን
- 1. በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
- 2. ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤
- 3. እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ
- 4. የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡
- 5. አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
- 6. ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡
- 7. የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡