37. سورة الصافات - ቁርዓን
- 1. መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡
- 2. መገሠጽንም በሚገሥጹት፤
- 3. ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡
- 4. አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡
- 5. የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡
- 6. እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡
- 7. አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡
- 8. ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡
- 9. የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡
- 10. ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡
- 11. ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡
- 12. ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡
- 13. በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡
- 14. ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡
- 15. ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
- 16. «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?
- 17. «የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡
- 18. «አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡
- 19. እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡
- 20. «ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡
- 21. «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡
- 22. (ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡
- 23. «ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡
- 24. «አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡
- 25. (ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡
- 26. በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡
- 27. የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡
- 28. (ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡
- 29. (አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡
- 30. «ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡
- 31. «በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡
- 32. «ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡
- 33. ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡
- 34. እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡
- 35. እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡
- 36. እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡
- 37. አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡
- 38. እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡
- 39. ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡
- 40. ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡
- 41. እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡
- 42. ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤
- 43. በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡
- 44. ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡
- 45. ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡
- 46. ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡
- 47. በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡
- 48. እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡
- 49. እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡
- 50. የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡
- 51. ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡
- 52. «በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡
- 53. «በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡
- 54. እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡
- 55. ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡
- 56. ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡
- 57. «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡»
- 58. (የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን?
- 59. «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡
- 60. ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
- 61. ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡
- 62. በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
- 63. እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡
- 64. እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡
- 65. እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡
- 66. እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡
- 67. ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡
- 68. ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡
- 69. እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡
- 70. እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡
- 71. ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡
- 72. በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡
- 73. የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
- 74. ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
- 75. ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን!
- 76. እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡
- 77. ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤
- 78. በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡
- 79. «በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡»
- 80. እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
- 81. እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡
- 82. ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡
- 83. ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡
- 84. ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡
- 85. «ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡
- 86. «ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?
- 87. «በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡
- 88. በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡
- 89. «እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡
- 90. ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡
- 91. ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?»
- 92. «የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?»
- 93. በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡
- 94. ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡
- 95. አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?»
- 96. «አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡»
- 97. «ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡
- 98. በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡
- 99. አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»
- 100. ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡
- 101. ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡
- 102. ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
- 103. ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡
- 104. ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!
- 105. ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
- 106. ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡
- 107. በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡
- 108. በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡
- 109. ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡
- 110. እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
- 111. እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡
- 112. በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡
- 113. በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡
- 114. በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡
- 115. እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡
- 116. ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡
- 117. በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡
- 118. ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡
- 119. በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡
- 120. ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡
- 121. እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
- 122. ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡
- 123. ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
- 124. ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን?
- 125. በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን?
- 126. አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)?
- 127. አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡
- 128. ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
- 129. በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡
- 130. ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡
- 131. እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
- 132. እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡
- 133. ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
- 134. እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡
- 135. (በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡
- 136. ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡
- 137. እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡
- 138. በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን?
- 139. ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
- 140. ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
- 141. ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡
- 142. እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡
- 143. እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤
- 144. እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡
- 145. እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡
- 146. በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡
- 147. ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡
- 148. አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡
- 149. (የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?»
- 150. ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?
- 151. ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡-
- 152. «አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡
- 153. በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን?
- 154. ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
- 155. አትገነዘቡምን?
- 156. ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን?
- 157. «እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡
- 158. በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡
- 159. አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
- 160. ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡
- 161. እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤
- 162. በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡
- 163. ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡
- 164. (ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡
- 165. እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡
- 166. እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡
- 167. እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡-
- 168. «ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤
- 169. «የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡»
- 170. ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
- 171. (የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡
- 172. እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
- 173. ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
- 174. ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡
- 175. እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡
- 176. በቅጣታችንም ያቻኩላሉን?
- 177. በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
- 178. እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡
- 179. ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡
- 180. የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
- 181. በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤
- 182. ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡