100. سورة العاديات - ቁርዓን
- 1. እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡
- 2. (በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤
- 3. በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤
- 4. በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤
- 5. በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡
- 6. ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡
- 7. እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡
- 8. እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡
- 9. (ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤
- 10. በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡
- 11. ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡