81. سورة التكوير - ቁርዓን
- 1. ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤
- 2. ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤
- 3. ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤
- 4. የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤
- 5. እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤
- 6. ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤
- 7. ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤
- 8. በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤
- 9. በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤
- 10. ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤
- 11. ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤
- 12. ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤
- 13. ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤
- 14. ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤
- 15. ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡
- 16. ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡
- 17. በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤
- 18. በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡
- 19. እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡
- 20. የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡
- 21. በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡
- 22. ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡
- 23. በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡
- 24. እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡
- 25. እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡
- 26. ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ?
- 27. እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
- 28. ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡
- 29. የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡