95. سورة التين - ቁርዓን
- 1. በበለስና በዘይት ወይራ እምላለሁ፡፡
- 2. በሲኒን ተራራም፤
- 3. በዚህ በጸጥተኛው አገርም (እምላለሁ)፡፡
- 4. ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡
- 5. ከዚያም (ከፊሉን) ከዝቅተኞች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው፡፡
- 6. ግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ለእነርሱ ተቆራጭ ያልኾነ ምንዳ አልላቸው፡፡
- 7. ታዲያ ከዚህ በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?
- 8. አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? (ነው)፡፡