99. سورة الزلزلة - ቁርዓን
- 1. ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤
- 2. ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤
- 3. ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤
- 4. በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡
- 5. ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡
- 6. በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡
- 7. የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
- 8. የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡