87. سورة الأعلى - ቁርዓን
- 1. ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡
- 2. የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡
- 3. የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡
- 4. የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡
- 5. (ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡
- 6. (ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡
- 7. አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡
- 8. ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡
- 9. ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡
- 10. (አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡