88. سورة الغاشية - ቁርዓን
- 1. የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን?
- 2. ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡
- 3. ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡
- 4. ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡
- 5. በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡
- 6. ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡
- 7. የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡
- 8. ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡
- 9. ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡
- 10. በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡
- 11. በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡
- 12. በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡
- 13. በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡
- 14. በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡
- 15. የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡
- 16. የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡
- 17. (ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
- 18. ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!
- 19. ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
- 20. ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)
- 21. አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡
- 22. በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡
- 23. ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤
- 24. አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
- 25. መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡
- 26. ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡