86. سورة الطارق - ቁርዓን
- 1. በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡
- 2. የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
- 3. ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡
- 4. ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
- 5. ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡
- 6. ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡
- 7. ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡
- 8. እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
- 9. ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡
- 10. ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡
- 11. የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡
- 12. (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤
- 13. እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡
- 14. እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡
- 15. እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡
- 16. (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡
- 17. ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡