92. سورة الليل - ቁርዓን
- 1. በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡
- 2. በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡
- 3. ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡
- 4. ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡
- 5. የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡
- 6. በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤
- 7. ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
- 8. የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤
- 9. በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤
- 10. ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
- 11. በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡
- 12. ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡
- 13. መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡
- 14. የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡
- 15. ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡
- 16. ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡
- 17. አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡
- 18. ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡
- 19. ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡
- 20. ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡
- 21. ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡