84. سورة الإنشقاق - ቁርዓን
- 1. ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤
- 2. ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
- 3. ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
- 4. በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤
- 5. ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡
- 6. አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡
- 7. መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤
- 8. በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡
- 9. ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡
- 10. መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤
- 11. (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡
- 12. የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡
- 13. እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡
- 14. እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡
- 15. አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡
- 16. አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡
- 17. በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤
- 18. በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡
- 19. ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡
- 20. የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?
- 21. በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?)
- 22. በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡
- 23. አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡
- 24. በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡
- 25. ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡