55. سورة الرحمن - ቁርዓን
- 1. አል-ረሕማን፤
- 2. ቁርኣንን አስተማረ፡፡
- 3. ሰውን ፈጠረ፡፡
- 4. መናገርን አስተማረው፡፡
- 5. ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡
- 6. ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡
- 7. ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡
- 8. በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡
- 9. መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡
- 10. ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡
- 11. በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡
- 12. የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡
- 13. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 14. ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡
- 15. ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡
- 16. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 17. የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡
- 18. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 19. ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡
- 20. (እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡
- 21. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
- 22. ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡
- 23. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 24. እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡
- 25. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 26. በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡
- 27. የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡
- 28. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 29. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡
- 30. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
- 31. እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡
- 32. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 33. የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)
- 34. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 35. በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡
- 36. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 37. ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡
- 38. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 39. በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡
- 40. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 41. ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡
- 42. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡
- 43. ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡
- 44. በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡
- 45. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 46. በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡
- 47. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 48. የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡
- 49. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 50. በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡
- 51. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 52. በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡
- 53. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 54. የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡
- 55. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 56. በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡
- 57. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 58. ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡
- 59. ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 60. የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?
- 61. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 62. ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡
- 63. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?›
- 64. ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡
- 65. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 66. በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡
- 67. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 68. በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡
- 69. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 70. በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡
- 71. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 72. በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡
- 73. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 74. ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡
- 75. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ?
- 76. በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡
- 77. ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
- 78. የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡