104. سورة الهمزة - ቁርዓን
- 1. ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡
- 2. ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ ፤(ወዮለት)፡፡
- 3. ገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡
- 4. ይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት) ውስጥ በእርግጥ ይጣላል፡፡
- 5. ሰባሪይቱም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
- 6. የተነደደችው የአላህ እሳት ናት፡፡
- 7. ያቺ በልቦች ላይ የምትዘልቅ የኾነችው፡፡
- 8. እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋጀች ናት፡፡
- 9. በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ (የተዘጋች ናት)፡፡