96. سورة العلق - ቁርዓን
- 1. አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
- 2. ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
- 3. አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
- 4. ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
- 5. ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
- 6. በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
- 7. ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
- 8. መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
- 9. አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
- 10. ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
- 11. አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
- 12. ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
- 13. አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
- 14. አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
- 15. ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
- 16. ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
- 17. ሸንጎውንም ይጥራ፡፡
- 18. (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
- 19. ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡