101. سورة القارعة - ቁርዓን
- 1. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤
- 2. ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት!
- 3. ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
- 4. ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤
- 5. ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡)
- 6. ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤
- 7. እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡
- 8. ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤
- 9. መኖሪያው ሃዊያህ ናት
- 10. እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
- 11. (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡