18. سورة الكهف - ቁርዓን
- 1. ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ መጣመምን ያላደረገበት ሲሆን በባሪያው ላይ ላወረደው ይገባው፡፡
- 2. ቀጥተኛ ሲሆን ከእርሱ ዘንድ የኾነን ብርቱን ቅጣት ሊያስፈራራበት፣ እነዚያንም በጎ ሥራዎችን የሚሠሩትን ምእመናን ለነሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን ሊያበስርበት፤ (አወረደው)፡፡
- 3. በእርሱ ውስጥ ዘለዓለም የሚቆዩበት ሲኾኑ (ያላቸው መኾኑን)፡፡
- 4. እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል» ያሉትን ሊያስፈራራበት (አወረደው)፡፡
- 5. ለእነሱም ለአባቶቻቸውም በርሱ ምንም እውቀት የላቸውም፡፡ ከአፎቻቸው የምትወጣውን ቃል ምን አከበዳት! ውሸትን እንጂ አይናገሩም፡፡
- 6. በዚህም ንግግር (በቁርኣን) ባያምኑ በፈለጎቻቸው ላይ በቁጭት ነፍስህን አጥፊ ልትሆን ይፈራልሃል፡፡
- 7. እኛ ማንኛቸው ሥራው ያማረ መኾኑን ልንፈትናቸው በምድር ላይ ያለን ሁሉ ለእርሷ ጌጥ አደረግን፤
- 8. እኛም በእርሷ ላይ ያለውን (በመጨረሻ) በእርግጥ በቃይ የሌለበት ምልጥ ዐፈር አድራጊዎች ነን፡፡
- 9. የዋሻውና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራቶቻችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን