82. سورة الإنفطار - ቁርዓን
- 1. ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
- 2. ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤
- 3. ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤
- 4. መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤
- 5. ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡
- 6. አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
- 7. በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡
- 8. በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡
- 9. ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡
- 10. በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤