90. سورة البلد - ቁርዓን
- 1. በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡
- 2. አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡
- 3. በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡
- 4. ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
- 5. በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?
- 6. «ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡
- 7. አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?
- 8. ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?
- 9. ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡
- 10. ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?
- 11. ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡
- 12. ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
- 13. (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡
- 14. ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡
- 15. የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤
- 16. ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡
- 17. (ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡
- 18. እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
- 19. እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
- 20. በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡