93. سورة الضحى - ቁርዓን
- 1. በረፋዱ እምላለሁ፡፡
- 2. በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤
- 3. ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡
- 4. መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡
- 5. ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡
- 6. የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡
- 7. የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡
- 8. ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡
- 9. የቲምንማ አትጨቁን፡፡
- 10. ለማኝንም አትገላምጥ፡፡
- 11. በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡